am_tn/pro/01/07.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

አባት ልጁን ያስተምራል፡፡

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው

“ፍርሀት”፣ “መጀመሪያ” እና “ጥበብ” የሚሉት ረቂቅ ስሞች እንደ ግስ መቅረብ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበብ ምን እንደሆነ ማወቅ ከመጀመርህ በፊት እግዚአብሔርን መፍራት አለብህ” ወይም “ጥበብ ምን እንደሆነ ለመማር መጀመሪያ እግዚአብሔርን ማክበር እና መታዘዝ አለብህ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ

ይህ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ውስጥ ለህዝቡ የገለጠላቸው ስሙ ነው፡፡ ይህንን እንዴት መተርጎም እንደሚገባ ለመረዳት ስለ ያህዌ የሚናገረውን የትርጉም ቃል ገፅ ላይ ይመልከቱ፡፡

ሞኞች ጥበብን እና ተግሳፅን ይንቃሉ

ለጥበብ እና ለምክር ዋጋ የማይሰጡ ሞኞች ናቸው፡፡

አትተወው

ይህ ፈሊጥ “ችላ አትበለው” ወይም “አትናቀው” ማለት ነው (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ለራስህም የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ውበት የሚሰጥ ጌጥ ይሆንሃልና

ወላጆች ለልጆቻቸው የሚያስተምሩት መመሪያ እና ተግሳፅ በጣም ጠቃሚ እና ትልቅ ዋጋ ያለው ስለሆነ እንደ ቆንጆ አንገት ላይ የሚደረግ ጌጥ ወይም የአበባ ጉንጉን ተደርገው ተገልፀዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- የአበባ ጉንጉን በራስ ላይ ወይም ድሪ በአንገት ላይ ማድረግ ውበትን እንደሚሰጥ እንደዚሁ እነርሱ ጠቢብ ያደርጉሀል (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አክሊል

ከአበባ ወይም ከቅጠል ተሰካክቶ የተሰራ ክብ ቅርፅ ያለው ዘውድ

ድሪ

በአንገት ዙሪያ የሚደረግ ጌጥ