am_tn/pro/01/04.md

1.7 KiB

በተጨማሪ ለአላዋቂዎች ጥበብ ለመስጠት ነው

ይህን ለውጦ “ጥበብ” የሚለውን ረቂቅ ስም እንደ ቅፅል “ጠቢብ” ብሎ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ይህ ደግሞ እንደ ገቢር/አድራጊ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ደግሞ ለአላዋቂዎች እንዴት ጠቢብ መሆን እንደሚቻል ለማስተማር ነው” (ረቂቅ ስሞች እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገቢሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

አላዋቂ

ልምድ የሌለው ወይም የአእምሮ ብስለት የሌለው

እውቀት እና ጥንቃቄን ለወጣቶች ለመስጠት

“እውቀት” እና “ጥንቃቄ” የሚሉት ረቂቅ ስሞች እንደ ግስ መቅረብ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ወጣቶች ማወቅ የሚገባቸውን እና ማድረግ የሚገባቸውን ትክክለኛውን ነገር እንዴት መወሰን እንዳለባቸው ለማስተማር ነው (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ጥንቃቄ

በእያንዳንዱ ሁኔታ ምን መደረግ እንዳለበት ለማወቅ

ጥበበኛ ሰዎች ያድምጡ፣ እውቀትንም ይጨምሩ

“ጠቢቦች ያስተውሉ፣ ተጨማሪ እውቀትን ያግኙ”

አስተዋዮች ምሪት ያግኙ

“አስተዋይ ሰዎች ከእነኚህ ምሳሌዎች እንዴት ጥሩ ውሳኔ መወሰን እንዳለባቸው ይማሩ”

እንቆቅልሾች

አንድ ሰው ስለ እነርሱ ካሰላሰለ በኋላ ብቻ ሊረዳቸው የሚችላቸው አባባሎች