am_tn/num/32/13.md

2.2 KiB

የእግዚአብሔርም ቁጣ በእሥራኤል ላይ ነደደ

እግዚአብሔር መናደዱን ለመግለፅ ልክ እሣት መቀጣጠል ከመጀመር ጋር ተመሳስሎ ነው የተነገረው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር በእሥራኤል ላይ በጣም ተናደደ”(ምሣሌያዊ አነጋገርና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

አርባ ዓመት

“40 ዓመት”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ትውልድ ሁሉ…ፊት እስኪጠፉ ድረስ

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ትውልዱን ሁሉ አጠፋ…ፊት”ወይም “ትውልዱ ሁሉ…በእግዚአብሔር ፊት ጠፋ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

በፊቱ ክፉ ያደረጉትን

በአንድ ሰው ፊት ማለት ሰውዬው ሊያየው በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ መሆን ማለት ነው፡፡“በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ያደረገ”ወይም “የእግዚአብሔር ሕልውና ባለበት ክፉ ነገርን ያደረገ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአባቶቻችሁ ፋንታ ቆማችኋል

የሮቤልና የጋድ ሰዎች ልክ የአባቶቻቸውን ሥራ ማድረጋቸው አባቶቻቸው ባደረጉት ሥፍራ ላይ እንደቆሙ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እንደ አባቶቻችሁ ማድረግ ጀምራችኋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔርን መዓት በእሥራኤል ላይ ትጨምሩ ዘንድ

ሰዎች እግዚአብሔር የበለጠ እየተናደደ እንዲሄድ የሚያደርጉት ድርጊት ልክ ሰዎች በእሣቱ ላይ ነዳጅ እንደሚጨምሩ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እግዚአብሔር በእሥራኤል ላይ የበለጠ እንዲናደድ ምክኒያት መሆን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህንን ሁሉ ሕዝብ

“ይሄ ሁሉ ሕዝብ”ወይም“ይሄ ሁሉ ትውልድ”