am_tn/num/31/52.md

1.9 KiB

ሻለቆችም የመቶ አለቆችም ለእግዚአብሔር የማንሣት ቁርባን ያቀረቡት ወርቅ ሁሉ አሥራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሰቅል ይመዝናል

“የሻለቆችቹና የመቶ አለቆቹ ለእግዚአብሔር የሰጡት የወርቅ ሥጦታ ሁሉ የመዘነው…”

ሻለቆችና የመቶ አለቆች

ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ሻለቆቹ ወይም የመቶ አለቆዎቹ የሚመሯቸው በሥራቸው የሚገኙ ሠራዊቶች ትክክለኛ ቁጥር ነው፡፡“1000 ሰራዊት የሚመሩ ሻለቃዎችና 100 ሠራዊት የሚመሩ መቶ አለቃዎች”ወይም 2/ “ሺዎችና መቶዎች የሚሉት ቃላት የታላላቅና የአነስተኛ የጦር ክፍሎች ስያሜዎች ናቸው እንጂ የሠራዊቱን ትክክለኛ ቁጥር የሚያመለክቱ አይደሉም” “ሠፊ የጦር ክፍል ያላቸው ሻለቃዎችና አነስተኛ የጦር ክፍል ያላቸው መቶ አለቃዎች” ይህንንተመሳሳይ ሐረግ በዘኁልቁ 31፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

16,750

“አሥራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ሰቅል

አንድ ሰቅል 11 ግራም ነው፡፡(መፅሐፍ ቅዱሣዊ ገንዘብ የሚለውን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር ፊት ለእሥራኤላውያን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ

ወርቆቹ መታሰቢያ የሚሆኑት እግዚአብሔር ድል የሰጣቸው መሆኑን ለማሳሰብ ነው፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በምድያማውያን ላይ ሕዝቡ የበቀል እርምጃ የወሰደ መሆኑን እግዚአብሔር ያስበው ዘንድ ነው፡፡