am_tn/num/31/21.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

አልዓዛር ከሠልፍ የመጡትን ሰዎች ከጦርነት መልስ በኋላ በሕጉ ሥርዓት መሠረት እንዴት ንፁህ መሆን እንደሚገባቸው ያስተምራቸዋል፡

ወርቁን፤ብሩን፤ናሱን፤ብረቱን፤ቆርቆሮውን፤አረሩን

በዚያን ወቅት ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ ብረቶች፡፡

በእሣት ውስጥ ለማለፍ የሚችለውን

“የማይቃጠለውን”

በእሣት ውስጥ ታሳልፉታላችሁ

“እሣት ውስጥ አሰቀምጡት”

የማንፃት ውኃ

ይሄ የሚያመለክተው አንድ ሰው ከኃጢአት ቁርባን የወሰደውን ውኃ ከአመድ ጋር የመደባለቁን ሁኔታ ነው፡፡(ኦሪት ዘኁልቁ 19፡17-19)

ከዚያ በኋላ ንፁህ ትሆናላችሁ

እነዚህ በሚከናወኑ ሥርዓቶች በእግዚአብሔር ፊት ንፁህ ሆኖ የመገኘት ልማዶች ናቸው፡፡