am_tn/num/30/01.md

2.2 KiB

ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል ወይም ራሱ በመሐላ ቢያስር

እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በጋራ እንዲቀርቡ የተደረጉት ስለ ስእለትና ስለ መሐላ አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ራሱ በመሐላ ቢያስር

ሙሴ እዚህ ላይ የሚናገረው አንድ ሰው አንድ ነገር ለማድረግ ቃል የመግባቱን ጉዳይ አስመልክቶ ቢሆንም የሚገባው ቃል ቁሣቁስ ይመስል ራሱ ላይ እንደሚያስረው ዓይነት አድርጎ ያቀርበዋል፡፡“አንድ ነገር ለመፈፀም ራስን መሥጠት”ወይም “አንድን ነገር ለመፈፀም ቃል መግባት” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቃሉን አይስበር፤ከአፉ እንደወጣው ሁሉ ያድርግ

እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በጋራ እንዲቀርቡ የተደረጉት የገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ እንደሚኖርበት አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ቃሉን አይስበር

“ቃሉን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰውዬውን መሐላና ቃል ኪዳን መግባት ነው፡፡ሙሴ እነዚሀን ነገሮች ተግባራዊ አለማድረግን ልክ አንድን ዕቃ ከመስበር ጋር አመሳስሎ ነው የሚናገረው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ከአፉ እንደወጣው ሁሉ

እዚህ ላይ“አፍ”የሚለው ቃል ሰውዬው የሚናገረውን ነገር ለመግለፅ የዋለ ነው፡፡“አደርገዋለሁ የሚለውን ነገር ሁሉ ማድረግ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)