am_tn/num/29/06.md

1.9 KiB

በሰባተኛው ወር..በወራቶቹ የመጀመሪያው ቀን

“በ7ኛ ወር…በእያንዳንዱ ወር በ1ኛው ቀን”“ወር”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የዕብራውያንን የወር አቆጠጠር ነው፡፡(የዕብራውያን ወራትንናተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)

በየወሩ፤የተለየ የሚቃጠል መሥዋዕት …ከእርሱ ጋር

“በየወሩ፤የተለየ የሚቃጠል መሥዋዕት …ከእርሱ ጋር” ይሄ በየወሩ መጀመሪያ ላይ የሚደረግ መሥዋዕት ነው፡

በዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፤ከመጠጡም ቁርባን

ይሄ የሚያመለክተው ካህናቱ በየዕለቱ መሥጠት የሚገባቸውን መሥዋዕት ነው፡፡የእህል ቁርባኑና የመጠጡቁርባን ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡“ዘወትር የሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት አብረው ከሚቀርቡት ከእህል ቁርባንና ከመጠጥ ቁርባን ጋር”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)

የተደነገገውን ትዕዛዝ ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእግዚብሔርን ትዕዛዝ ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ”ወይም “እግዚአብሔር ያዘዘውን ትዕዛዝ ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእግዚአብሔር በእሣት የሚቀርብ

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር ያቃጠላችሁት ቁርባን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)