am_tn/num/29/01.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡

በሰባተኛውም ወር ከወሩ በመጀመሪያ ቀን

ይሄ የሚያመለክተው የዕብራውያንን ሰባተኛ ወር ነው፡፡“በ1ኛው ወር በ7ኛው ወር”(የዕብራውያን ወራትንናተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን ለማክበር የተቀደሰ ጉባዔ ይሁንላችሁ

“እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማክበር በአንድነት ተሰብሰቡ” “የተቀደሰ ጉባዔ”የሚለው ቃል ሰዎች እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚሰበሰቡበት ሁኔታ ማለት ነው፡፡እግዚአብሔርን ማምለክ የተቀደሰ ክስተት ነው፡፡

እናንተ መለከቶችን የምትነፉበት ቀን ነው

“እናንተ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እዚህ ላይ የእሥራኤልን ሕዝብ የሚወክሉትን ካህናትን ነው፡፡ካህናት አምልኮው እንዲጀመር መለከትን ይነፋሉ ወይም ማህረሰቡ በአንድነት እንዲሰባሰብ ለማድረግ፡፡“ካህናት መለከቶችን የሚነፉበት ቀን ይሆናል”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)