am_tn/num/28/29.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡

ከመሥፈሪያው አንድ አሥረኛ እጅ

“አንድ አሥረኛ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች አንዱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ሁለት ሊትር”ወይም “ከመሥፈሪያው አንድ አሥረኛ እጅ”(ሁለት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)

በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እናንተ በዘይት የምትለውሱት መልካም ዱቄት” (ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

መሥዋዕትን ማቅረብ

“መሥዋዕት ማቅረብ”የሚለው ሐረግ “መሰዋት”በሚለው ሥም ሊገለፅ ይችላል፡፡(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)

የእነርሱን የመጠጥ ቁርባን

“የእነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እያንዳንዱ እንስሳ በሚሰዋበት ወቅት አብረው መቅረብ የሚገባቸውን የመጠጥ ቁርባኖችን ነው፡፡“ከአነርሱ ጋር አብረው የሚቀርቡት የመጠጥ ቁርባኖች”ወይም “የሚያጅቧቸው የመጠጥ ቁርባኖች”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)