am_tn/num/28/16.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡

በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን….ከዚህም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን

“በመጀሪያው ወር በወሩ በ14ኛው ቀን…በዚሁ ወር በ15ኛው ቀን” “ይሄ የሚያመለክተው የመጀመሪያውን የዕብራውያንን ወር ነው” (የዕብራውያን ወራትናተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው

“የእግዚአብሔርን ፋሲካ ልታከብሩት ይገባል”

በዓል ይሆናል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዓል ልታደርጉ ይገባል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሾ የሌለው ቂጣ መበላት ይኖርበታል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እርሾ የሌለው ቂጣ ልትበሉ ይገባል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

በመጀመሪያው ቀን

ይሄ የሚያመለክተው የበዓሉን የመጀመሪያ ዕለት ነው፡፡ይሄ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“በበዓሉ በ1ኛው ቀን” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን ለማክበር የተቀደሰ ጉባዔ መደረግ ይኖርበታል

“እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማክበር መሰብሰብ ይኖርባችኋል፡፡” “የተቀደሰ ጉባዔ”የሚለው ሐረግ ሰዎች ተሰብስበው እግዚአብሔርን ሲያመልኩ ማለት ነው፡፡እግዚአብሔርን ማምለክ የተቀደሰ ክስተት ነው፡፡