am_tn/num/27/15.md

1.6 KiB

የሥጋ ሁሉ መንፈስ አምላክ እግዚአብሔር

ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/እዚህ ላይ “መንፈስ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሕዝብን ሁሉ ነው፡፡“የሰው ዘር ሁሉ የበላይ የሆነው እግዚአብሔር”ወይም 2/“መንፈስ”የሚለው ቃልየሚያመለክተው እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ሕይወትንና ትንፋሽን መሥጠቱን ነው፡፡ “ለሰው ሁሉ ትንፋሽን የሚሰጠው እግዚአብሔር”ወይም“ለሰው ሁሉ ሕይወትን የሚሰጠው እግዚአብሔር”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)

በማህበሩ ላይ

በተወሰኑ ሰዎች “ላይ”መሆን ማለት እነርሱን ለመምራት ሥልጣን መያዝ ማለት ነው፡፡“ማህበሩን የሚመራ ሰው”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በፊታቸው የሚወጣውን፤በፊታቸውም የሚገባውን፤የሚያስወጣቸውንም የሚያስገባቸውንም ሰው

ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ሕዝቡን የሚመራና በጦርነትም ወቅት ሠራዊቱን የሚመራ ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር መንጋ እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን

ይሄ ንፅፅር ሲሆን የዚህ ሃሣብ ትርጉም ሕዝቡ መሪ የማይኖረው ከሆነ የተቅበዘበዘና ደካማ ይሆናል ማለት ነው፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)