am_tn/num/27/04.md

1.1 KiB

ወንድ ልጅ ባይኖረው የአባታችን ስም ከወገኑ መካከል ለምን ይጠፋል?

በዚያን ዘመን መሬት የመውረስ ሥልጣን የነበረው ወንድ ልጅ ብቻ ነበር፡፡ሴቶቹ ይህንን ጥያቄ የጠየቁት ውርሱን በመውረስ የዘር ሐረጉ እንዲቀጥል ለማስቻል ነበር፡፡ይሄ እንደ መግለጫ ሊፃፍ ይችላል፡፡“አባታችን ወንድ ልጅ ስለሌለው ብቻ የአባታችንን ሥም ከነገድ አባልነቱ ልትፍቁት አይገባም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስትን ስጠን

ይሄ የአባታቸው ዘመዶች በወረሱት ርሰት አካባቢ የሚወርሱት ርስት ይሰጣቸው ዘንድ ያቀረቡት ጥያቄ ነው፡፡የዚህ ፍቺ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“የአባታችን ዘመዶች ባሉበት ሥፍራ ላይ ርስትን ሥጠን”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)