am_tn/num/26/60.md

1.7 KiB

ናዳብ…አብዮድ…ኢታምር

የእነዚህን ሰዎች ሥም በዘኁልቁ 3፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የሌለውን እሳት አቀረቡ

እዚህ ላይ“እሣት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው “የሚቃጠል መሥዋዕትን”ነው፡፡ተመሳሳይ የሆነውን ሐረግ በዘኁልቁ 3፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“እርሱ ባልተቀበለው ሁኔታ የሚቃጠል መሥዋዕትን አቀረቡ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

የተቆጠሩት

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“መሪዎቹ የቆጠሯቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ሃያ ሶስት ሺህ

“23,000”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያ በላይ ያሉ

“አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለው”

ርሰት አልተሰጣቸውም ነበር

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡እዚህ ላይ “ርስት”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተወረሰውን መሬት ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ምንም ዓይነት መሬት በርስትነት እአይሰጣቸውም አለ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)