am_tn/num/24/17.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በለዓም ከአራቱ ትንቢቶች መካከል አንዱን መናገር ይጀምራል፡፡

እርሱን አየዋለሁ አሁን ግን አይደለም፤እርሱን እመለከተዋለሁ በቅርብ ግን አይደለም

እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡በለዓም ወደፊት ስለሚከሰተው ነገር ራዕይ አየተመለከተ ነው፡፡“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የወደፊቱን የእሥራኤል መሪ ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል

እዚህ ላይ“ኮከብ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በእሥራኤል ላይ ሥልጣን የሚይዘውን ንጉሥ ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ቋንቋ የሚለውን ይመልከቱ)

ከያዕቆብ

እዚህ ላይ“ያዕቆብ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የያዕቆብን ትውልድ ነው፡፡“ከያዕቆብ ትውልድ መካከል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ከእሥራኤል በትር ይነሳል

ይሄ ከመጀመሪው ዓረፍተ ነገር ጋር ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያለው፡፡እዚህ ላይ “በትር”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ብርቱ የሆነ ንጉሥን ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ከእሥራኤል

እዚህ ላይ“እሥራኤል”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የወደፊት እሥራኤላውያንን ነው፡፡“ወደፊት ከሚወለዱት እሥራኤላውያን መካከል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

የሞዓብንም ማዕዘኖች ይመታል

ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/ሞዓብ መሪዎችን አናት ይመታል2/የሞዓብን መሪዎች ያጠፋል፡፡

የሤትንም ልጆች

ይሄ የሤት ዝርያዎች የሆኑ ሞአባውያንን የሚመለከት ነው፡፡