am_tn/num/24/15.md

1002 B

የቢዖር ልጅ በለዓም

ቢዖር በለዓም አባት ነበረ፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

ዓይኖቹም የተከፈቱለት

ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው በሚገባ የሚያይና የሚረዳ መሆኑን ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 24፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የልዑልንም ዕውቀት የሚያውቅ

“ዕውቀት”የሚለው ረቂቅ ሥም በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ታላቁ እግዚአብሔር የገለጠለትን ነገር የሚያውቅ ሰው”(አሕፅሮተ ሥሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ይሰግዳል

ይሄ ለእግዚአብሔር የመገዛት ምልክት ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)