am_tn/num/24/07.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በለዓም በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ሆኖ ትንቢት መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ውኃ ይፈስሳል…በብዙ ውኆች ይሆናል

ብዛት ያለው ውኃ በምድር ላይ እንዳሉና እግዚአብሔር እንደባረካቸው ሰብሎች ተቆጥሯል፡፡“እግዚአብሔር ለሰበሎቻቸው ይሆን ዘንድ ብዙ ውኃ በመሥጠት ይባርካቸዋል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ዘሩም በብዙ ውሆች ይሆናል

በሚገባ ውኃ የጠጣ ዘር የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተትረፈረፈ ሰብል ይኖራቸው ዘንድ የእግዚአብሔር በረከት በእነርሱ ላይ የሚመጣ መሆኑን ነው፡፡“ጤናማ የሆኑ ሰብሎችን ያበቅሉ ዘንድ ለሚዘሩት ዘር ከበቂ በላይ የሆነ ውኃን ያገኛሉ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ንጉሡም ከፍ ከፍ ይላል…መንግሥቱም ይከበራል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ከሌሎች አገራት ይልቅ እጅግ እንደሚባርካቸው አፅንዖት የሚሰጥ ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ንጉሥም ከአጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል

“ከፍ ከፍ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ታላቅ የሆነ ክብርና ሥልጣንን ነው፡፡ይሄ የሚያመለክተው ወደፊት የሚነሣው የእሥራኤል ንጉሥ ከአጋግ ይልቅ የበለጠ ክብርና ሥልጣን የሚኖረው መሆኑን ነው፡፡አጋግ የአማሌቃውያን ንጉሥ ነበር፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ))

መንግሥቱም ይከበራል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሌሎች ሰዎች ለመንግሥታቸው ክብርን ይሰጣሉ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)