am_tn/num/24/06.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በለዓም በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ሆኖ ትንቢት መናገሩን ይቀጥላል፡፡

በሸለቆዎች ተዘርግተዋል

በለዓም እሥራኤልን በሚመለከት ሸለቆዎቸን እንኳን መሸፈን እስኪችሉ ድረስ ዘንድ በቁጥር እጅግ ብዙ እንደሆኑ አድርጎ ነው የሚናገረው፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)

በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች

በለዓም እሥራኤላውያንን በቂ ውኃ እንደሚጠጡና የተትረፈረፈ ምርትን እንደሚያስገኙ አትክልቶች አድርጎ ያቀርባቸዋል፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር እንደተከለው እሬት

የእሬት አትከልቶች መልካም የሆነ ሽታ ያላቸው በደረቅ የአየር ሁኔታ ውስጥ እንኳን በሚገባ ማደግ የሚችሉ ናቸው፡፡በለዓም እሥራኤላውያን እንደ እሬት አትክልቶች እንደሚያድጉና መልካም እንደሚሆኑይናገራል፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር የተከለው እሬት”(ያልታወቁ ነገሮችን መተርጎም፤ተነፃፃሪ የሚለውንና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

በውኃም ዳር እንዳሉ ዘግባዎች

ዝግባ በእሥራኤል ውስጥ ከነበሩት ዛፎች ትልቁ ነው፡፡በለዓም እሥራኤላውያን ልክ ውኃ እንደሚጠጣ ዝግባ ዛፍ ግዙፍ ሆነው እንዳደጉ ዓይነት አድርጎ ይናገራል፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)