am_tn/num/24/04.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በለዓም በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ሆኖ ትንቢት መናገሩን ይቀጥላል፡፡

እርሱ ይናገራል…እርሱ ያያል…እርሱ ይሰግዳል

እዚህ ላይ በለዓም ራሱን የሚጠራው“እርሱ” እያለ ነው፡፡

እርሱ ይሰግዳል

ይሄ የትህትና ድርጊት ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ዓይኖቹ የተከፈቱለት

“ዓይኖቹ የተከፈቱለት”የሚለው ቃል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን በለዓም እግዚአብሔር መናገር የፈለገውን ነገር የማወቅ ችሎታ ተሰጥቶታል ለማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ያዕቆብ ሆይ ድንኳኖችህ፤እሥራኤል ሆይ ማደሪያዎችህ ምንኛ ያምራሉ?

እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡ለበለዓም የእሥራኤል ሰፈር ውብ እንደሆነበት አስረግጠው የሚናገሩ ናቸው፡፡ (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)