am_tn/num/24/02.md

1.1 KiB

ዓይኖቹን አነሳ

“ዓይኖቹን አነሳ”የሚለው ቃል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ወደ ላይ መመልከት ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ መጣ

ይሄ ማለት ትንቢትን መናገር ይችል ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረው ማለት ነው፡፡

ይህንን ትንቢት ተቀበለ

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ይህንን ትንቢት ሰጠው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

የቢዖር ልጅ በለዓም

ቢዖር የበለዓም አባት ነበር፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

ዓይኖቹ የተከፈቱለት

ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያሣየው በሚገባ ማየቱንና መገንዘቡን ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)