am_tn/num/23/23.md

1.1 KiB

በያዕቆብ ላይ አስማት የለም …በእሥራኤልም ላይ ምዋርት የለም

እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሣሣይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ማንም ሰው በእሥራኤል ላይ መርገምን ቢደርገ ሊሰራለት አይችልም ለማለት ነው፡፡“እዚህ ላይ ያዕቆብ የሚል ቃል የሚያመለክተው እሥራኤልን ነው” (ተመሳሳይነት የሚለውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ይባላል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች ሊናገሩ ይችሉ ይሆናል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ያደረገውን ተመልከቱ

እግዚአብሔር ለእነርሱ ያደረገላቸው ነገር መልካም መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡“እግዚአብሔር ለእነርሱ ያደረገላቸውን መልካም ነገር ተመልክቱ!”