am_tn/num/23/11.md

1.6 KiB

ባላቅ

ይሄ የሞአብ ንጉሥ ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

ያደረገህብኝ ምንድነው?

ባላቅ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው በለዓምን ለመውቀስ ነበር፡፡ይሄንን ጥያቄ በዓረፍተ ነገር መልክም መተርጎም ይቻላል፡፡“ይህንን በእኔ ላይ አድረገሃል ብዬ አላምንም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ተመልከት

ይሄ የሚያመለክተው የሚመጣውን አስደንጋጭ ድርጊት ነው፡፡

እግዚአብሔር በአፌ ያደረገውን እናገር ዘንድ አልጠነቀቅምን?

በለዓም ይሄንን አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ የሚጠይቀው ለድርጊቶቹ ምክኒያት ለመሥጠት ነው፡፡ይሄ በመግለጫ መልክ ሊተረጎም ይችላል፡“እግዚአብሔር የተናገረኝን ነገር ብቻ ለመናገር መጠንቀቅ አለብኝ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር በአፌ ያስቀመጠውን ነገር ብቻ እናገር ዘንድ

መልዕክቱ እገዚአብሔር በአፍ ውሰጥ እንደሚያስቀምጠው ዓይነት ነገር ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡ይህንንተመሳሳይ ሐረግ በዘኁልቁ 22፡38 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“እግዚአብሔር የሚናገረኝን ብቻ ለመናገር”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)