am_tn/num/21/24.md

1.9 KiB

እሥራኤልም መታ

እዚህ ላይ “እሥራኤል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡“እሥራኤላውን ጥቃት አደረሱ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

በሠይፍ ሥለት

“ስለታም በሆነው የሠይፉ ክፍል” “የሠይፍ ሥለት”የሚለው ቃል የሚያያዘው ከሞትና ፍፁም ከሆነ ጥፋት ጋር ነው፡፡“ሙሉ በሙሉ ድል ነሷቸው”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

የእነርሱን ምድር ወረሱ

“የአሞራውያንን ምድር ድል አደረጉ” እዚህ ላይ “የእነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሞራውያንን ነው፡፡

የአሞን ሕዝብ…አሞራውያን

“አሞናውያን..አሞራውያን”ወይም “አሞን ሕዝብ ወይም የአሞር ሕዝብ” እነዚህ ስሞች ተመሳሳይ ቢሆኑም የሚያመለክቱት ግን ሁለት የተለያዩ ሕዝቦችን ነው፡፡

የተመሸገ ነበረ

“ጠንካራ የሆነ መከላከያ ነበረው” እሥራአላውያን አሞናውያንን አላጠቁም፡፡

በሐሴቦንና በመንደሮቹ ሁሉ

እዚህ ላይ“ሁሉ”የሚለው ቃል አካታች ሲሆን የሐሴቦን ከተማ በቅርብ ካሉት መንደሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ይገልፃል፡፡“ሐሴቦንና የሚቆጣጠራቸው በቅርብ የሚገኙ ከተሞች”

ሴዎን እርሱን ከተማዎች ሁሉ ወስዶ ነበር

እዚህ ላይ“የእርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሞአብን ንጉሥ ነው፡፡