am_tn/num/20/04.md

1.2 KiB

ማያያዣ ዓረፍተ ነገር

የእሥራኤል ሕዝብ በሙሴና በአሮን ላይ ማጉረምረማቸውን ይቀጥላሉ፡፡

የእግዚአብሔርን ሕዝብ ወደ ምድረ በዳ ለምን አመጣህ? እኛና ከብቶቻችን እንድንሞት ነውን?

ሕዝቡ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው በሙሴና በአሮን ላይ ለማጉረምርም ነው፡፡እንደ መግለጫ ሊታይ ይችላል፡፡“የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከከብቶቹ ጋር እንዲሞት ለማድረግ እዚህ በረሃ ውስጥ ማምጣት አልነበረብህም” (ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደዚህ አስከፊ ሥፍራ እንመጣ ዘንድ ከግብፅ ምድር ለምን አወጣኸን?

ሕዝቡ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው በሙሴና በአሮን ላይ ለማጉረምርም ነው::እንደ መግለጫ ሊታይ ይችላል፡፡“እኛን ወደዚህ አስከፊ ሥፍራ ለማምጣት ከግብፅ ምድር ልታወጣን አይገባህም ነበር”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)