am_tn/num/19/11.md

2.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

“ንፁሕ መሆን”እና “መቀደስ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘትን ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ

“ንፁሕ ያልሆነ”“መርከስ”“ቅድሰና ማጣት” እና “በኃጢአት መበከል”የሚሉት ሃሣቦች የሚያመለክቱት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለማግኘትን ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሞተውን ሰው በድን

“የማንኛውም ሰው ሬሣ”

ራሱን ያጠራል

ይሄ ሰው አንድ ንፁሕ የሆነ ሰው ይጠራና ከውኃ ጋር የተደባለቀ የጊደር አመድ በመርጨት እንዲያጠራው ይጋብዘዋል፡፡አንድን ሰው እንዲያጠራው በመጥራቱ ልክ ያ ሰው ራሱ እንደሚያጠራው ዓይነት ተደርጎ ነው የሚገለፀው፡፡“አንድን ሰው እንዲያጠራው መጋበዝ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

በሶስተኛው ቀን ራሱን ካላጠራ በሰባተኛው ቀንም ንፁሕ አይሆንም

ይሄ በአዎንታዊ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በሰባተኛው ቀን ንፁሕ የሚሆነው በሶስተኛው ቀን ራሱን ያጠራ እንደሆነ ብቻ ነው”(ድርብ አሉታዎች)

ያ ሰው ተለይቶ መጥፋት አለበት

“መጥፋት”የሚል ቃል የሚያመለክተው ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ማንኛውም ግንኙነት ተቋርጦ መባረሩን ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 9፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ያ ሰው መባረር አለበት”ወይም “ያንን ሰው ማባረር አለባችሁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ላይ ባለው ርኩሰት ላይ ውኃ አልተረጨምና

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ማንም ሰው በርኩሰቱ ላይ ውኃን አልረጨም”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

በርኩሰት ላይ የሚረጭ ውኃ

“የረከሱ ነገሮች እንዲነፁ ለማድረግ የሚረጭ ውኃ”ወይም“ነገሮችን ለማንፃት የሚረጭ ውኃ”

ርኩስ ይሆናል፤ርኩሰቱ ከእርሱ ጋር ይቆያል

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በአንድ ላይ እንዲነገሩ የተደረገው ለጉዳዩ አፅንኦት ለመስጠት ሲባል ነው፡፡ (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)