am_tn/num/18/19.md

2.6 KiB

ማያያዣ ዓረፍተ ነገር

እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ለአንተ ሰጥቼሃለሁ

እግዚአብሔር ይህንን ውሳኔ ቀድሞ የወሰነ በመሆኑ ጉዳዩን እንደፈፀመው ዓይነት አድርጎ ይናገራል፡፡“ለአንተ ሰጠሁህ”

ለልጆችህ እንደሚቀጥል ድርሻ

ድርሻ ማለት አንድ ሰው የተወሰነውን የአንድ ነገር ክፍል ሲወስድ ማለት ነው፡፡“በማይቋረጥ መልኩ እንደምትወስዱት ድርሻችሁ”

ከአንተም ጋር ለዘርህ የጨው ቃል ኪዳን ለዘለላም ነው

ሁለቱ ሐረጎች የሚያመለክቱት ተመሳሳይ የሆነ ነገርን ነው፡፡“እነዚህ ሐረጎች በጋራ በመሆን አፅንዖት የሚሰጡት ኪዳኑ ለዘላለም የሚፀና መሆኑን ነው፡፡”“ዘላለማዊ የሆነ ሥምምነት”(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

የዘላለም ጨው ቃል ኪዳን

“በጨው የተደረገ ቃል ኪዳን”ጨው ዘለቂነትን የሚያመለክት ሲሆን በመሥዋዕትና በቃል ኪዳን ወቅት በሚደረጉ ምግቦች ላይ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረግ ነበር፡፡”ዘላቂነት ያለው ኪዳን”ወይም “ዘላለማዊ ኪዳን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በምድራቸው ርስት በመካከላቸውም ድርሻ አይሆንልህም

እግዚአብሔር ሌሎች ሰዎች የሚይዙትን ምድር እንደሚወርሱት ዓይነት አድርጎ ይናገራል፡፡“ከሕዝቡ ምድር አንዱንም አትወርሱም” ወይም “እሥራኤላውያን ከሚይዟቸው መሬቶች ውስጥ አንዱንም አትወስዱም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ድርሻህና ርስትህ ርስት እኔ ነኝ

እግዚአብሔር አሮንና ዘሩ እርሱን በክህነት በማገልገላቸው የሚጠብቃቸውን ታላቅ ክብር ሲገልፅላቸው ልክ እግዚአብሔር ራሱን እንደሚወርሱት አድርጎ ነው የሚናገረው፡፡“በዚያ ምትክ የምኖራችሁ እኔ ነኝ”ወይም“በዚያ ምትክ እንድታገለግሉኝ እፈቅድላችኋለሁ፤በአገልግሎታችሁም ወቅት የሚያስፈልጋችሁን ነገር ሁሉ አዘጋጅላችኋለሁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)