am_tn/num/18/14.md

2.7 KiB

ማያያዣ ዓረፍተ ነገር

እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል

ማሕፀንን የሚከፍት ሁሉ፤በኩራት የሆነ ሁሉ

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡“ማሕፀንን የሚከፍት ወንድ ሁሉ”(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ማሕፀንን የሚከፍት ሁሉ

“ማሕፀን መክፈት”የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገርእናት የምትወለደው የመጀመሪያ ወንድ ልጇ ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በመጀመሪያ የተወለደውን ሁሉ ሰዎቸ ሊቤዡት ይገባል

መጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ልጃቸውን መሥዋዕት ከማድረግ ይልቅ ለልጆቻቸው ሲሉ ለካህኑ ገንዘብ መክፈል ነበረባቸው፡፡

ሰዎች ከተተቤዧቸው ከአንድ ወር በኋላ ተመልሰው ሊቤዡ ይገባል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንድ ወር ከሞላቸው በኋላ ሰዎች መልሰው ሊቤዧቸው ይገባል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ዳግም ሊቤዡ የሚገባቸው ነገሮች

ይሄ ምናልባት የሚያመለከተው ሰዎችን እንጂ ንፁሕ ያልሆኑ እንስሳትን ለማመልከት አይመስልም፡፡

አምስት ሰቅል …ሃያ አቦሊ

በዘመናዊ የመለኪያ መንገድ መተቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚሀን ተግባራዊ የማድረጊያ መንገዶች እነሆ፡፡“አምስት ብር ቁርጥራጮች….እያንዳንዱ አምስት ግራም ያህል የሚመዝን”ወይም“በቤተመቅደሱ ውስጥ ጥቅም ላይ ባሉት የጥራት ደረጃዎች መሠረት የሚመዝን አምሳ ግራም ብር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊመለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)

አምስት ሰቅል

ሰቅል የክብደት መለኪያ ነው፡፡የሚመዘነው ነገር ምን እንደሆነ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የቤተመቅደስሰቅል

የተለያየ ዓይነት የሰቅል ዓይነቶች ነበሩ፡፡ይሄኛው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በሚገኘው የተቀደሰው ሥፍራ ላይ ሰዎች የሚጠቀሙበት ዓይነት ነበር፡፡ሃያ አቦሊ ይመዝን ነበር፡፡ይሄ 11 ግራም ገደማ ይሆናል፡፡(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)