am_tn/num/18/03.md

2.1 KiB

የዓረፍተ ነገር ማያያዣ

እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል፡፡

አንተን ማገልገል ይኖርባቸዋል..እነርሱበአንድነት ይሁኑ

“እነርሱ”የሚለው ቃል የሌዊ ነገድ አባላትን የሚያመለክት ሲሆን “አንተ”የሚለው ቃል ደግሞ የሚያመለክተው አሮንን ነው፡፡(አንተ/እናንተ የሚለው ቃል በተለያየ መንገድ የሚገለፅበት የሚለውን ይመልከቱ)

ወይም አንተና እነርሱ ትሞታላችሁ

እዚሀ ላይ “እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው“በቤተመቅደሱ ውስጥ ባሉት ሥፍራዎች ሁሉ”የመግባት መብት ያላቸውን ማንኛውንም የሌዊ ነገድ አባላትን ነው፡፡“እነርሱ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም አሮንንና በተፈቀደላቸው አገልግሎት ውስጥ የሚገኙትን ሌዋውያንን ነው፡፡“(ተውላጠ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)

ሌላ ሰው ወደ እናንተ አይቅረብ፡፡ኃላፊነቱን መውሰድ ይኖርባችኋል፡፡

እዚህ ላይ “እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር በመሆኑ የሚያመለክተው አሮንንና የተቀሩትን ሌዋውያን ነው፡፡(አንተ/እናንተ የሚለው ቃል በተለያየ መንገድ የሚገለፅበት የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣዬ በእሥራኤል ልጆች ላይ እንደገና እንዳይነድባቸው

ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ እጅግ እንደተቆጣ ያመለክታል፡፡2/“በእሥራኤል ሕዝብ ላይ ዳግም በእጅጉ እንዳልቆጣ”2/ይሄ የሚያሣየው ከመቆጣቱ የተነሣ መቅጣቱን ያመለክታል፡፡“የእሥራኤልን ሕዝብ ደግሜ እንዳልቀጣ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)