am_tn/num/16/33.md

1.3 KiB

ወደ ሲኦል ወረዱ

በኦሪት ዘኁልቁ 16፡30 ላይ ተመሳሳይ የሆነ ሐረግ ይገኛል፡፡እዚያ ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

እነርሱ ተደነቁ

“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው “እሥራኤላውያንን ሁሉ”ነው፡፡

ምድሪቱ እኛንም እንዳትውጠን

ሰዎቹ የሚናገሩት ልክ ምድር ሕይወት እንዳላት ነገር አድርገው ነው፡፡“ምናልባት መሬት ተከፍታ እኛንም ልትውጠን ትችላለች”ወይም “ምድር እንደገና የምትከፈት ከሆነ እኛም እዚያ ውስጥ ወድቀን ልንቀበር እንችላለን” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥታ ሁለት መቶ ሃምሳ ሰዎች በላች

በእሣት መጥፋታቸው ልክ በእሣት እንደተበሉ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡ “እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቶ 250 ሰዎች አጠፋ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

250 ሰዎች

“ሁለት መቶ ሃምሳ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)