am_tn/num/16/12.md

2.8 KiB

በምድረ በዳ ትገድለን ዘንድ …ያወጣኸን አይበቃህምን?

ዳታንና አቤሮን ይህንን ጥያቄ የሚጠይቁት ሙሴን ለመገሰፅ ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እኛን እዚህ ምድረ በዳ አምጥተህ በምድረ በዳ ልትገድለን ማሰብህን ምንም እንዳልሆነ ነገር ቆጥረኸዋል”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ትንሽ ነገር

“በቂ ያልሆነ”ወይም “ጠቃሚ ያልሆነ”

ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር

ምድሪቱ ለከብቶችና ለዕፅዋት ተስማሚ መሆኗን ለመግለፅ ከእነዚያ እንስሳት የሚገኘው ወተትና ማር ልክ በምድሪቱ ላይ እንደሚፈስስ ነገር አድርገው ይገልፁታል፡፡ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 14፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ከብቶችን ለማርባትና እህልን ለማብቀል እጅግ የያመች ሥፍራ ነው”ወይም “እጅግ ለም የሆነ መሬት ነው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ልትገድለን

ሰዎቹ ነገሩን አጋንነው የሚናገሩት ከአነርሱ ውስጥ አንድ ሰው ቢሞት ሙሴን ተጠያቂ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡(የተጋነነ ንፅፅር እና አጠቃላይነት የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ርስት

እግዚአብሔር ለዘላለም የሚሰጣቸውን ነገር በውርስ እንደሚያገኙት ነገር አድርገው ነው የሚናገሩት፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በባዶ ተስፋ ዓይኖቻችንን ታሳውራለህን?

ሰዎቹ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቁት ሙሴን ለመቃወም ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በባዶ ተስፋ ልታሳውረን ትፈልጋለህ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ልታሳውረን

ሰዎችን ማታለል ሰዎችን እንደ ማሳወር ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ልታታልለን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በባዶ ተስፋ

ተስፋ የተሰጣቸው ነገሮች ያለመከናወናቸውን ለመግለፅ ባዶ ከሆነ ዕቃ ማስቀመጫ ጋር ያነፃፅሩታል፡፡“የማትፈፅማቸው የተስፋ ቃሎችህ”ወይም “እነዚህ ነገሮች ይደረጋሉ እያልክ የማታከናውናቸው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)