am_tn/num/16/08.md

1.7 KiB

አይበቃችሁምን..እነርሱን ለማገልገል

ሙሴ ይህንን ጥያቄ የሚያነሣው ቀአትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመገሰፅ ብሎ ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እነርሱን ማገልገል ትንሽ ነገር መስሎ ይታያቸኋል”ወይም “እነርሱን ማገልገል እንደ ትንሽ ነገር መስሎ ሊታያችሁ አይገባም፡፡”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእናንተ ትንሽ ነገር

“ለእናንተ የማይበቃችሁ” ወይም “ለእናንተ ጠቃሚ ያልሆነ”

ክህነትንም ትፈልጋላችሁ

ክህነት መፈለግን ልክ በዓይናቸው እንደሚፈልጉት ዓይነት በሚመስል መልኩ ተገልጿል፡፡“ክሀነትን ትፈልጋላችሁ” ወይም “እናንተም ካህናት መሆን ትፈልጋላችሁ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን በሚያገለግለው በአሮን ላይ ለምን ታጉረመረማላችሁ?

ሙሴ ይህንን ጥያቄ የሚያነሳበት ምክኒያት የአሮንን መልካም የሆነ ድርጊት በመጥቀስ ለመሞገት ነበር፡፡ምክኒያቱ ደግሞ አሮን እግዚአብሔር አድርግ የሚለውን ነገር የሚያደረግ ሰው ሰለነበረ ነው፡፡“የምታጉመርሙት በአሮን ላይ ሣይሆን አሮንን በሚያዝዘው በእግዚአብሔር ላይ ነው”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)