am_tn/num/16/06.md

1.1 KiB

ማያያዣ ዓረፍተ ነገሮች

ሙሴ ለቀአትና ከቀአት ጋር ለነበሩት ሰዎች መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ጥና

ዕጣንን ለማጤስ የሚያገለግል ዕቃ፡፡

በእግዚአብሔር ፊት

ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“በእግዚአብሔር ሕልውና ፊት”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ያ ሰው ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ያንን ሰው ለራሱ የተለየ ያደርገዋል” (ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ እጅግ አብዝታችኋል

ይሄ የሚያመለከተው አንድ ሰው ማድረግ ከሚገባው በላይ አልፎ ማድረጉን ነው፡፡“ማድረግ ከሚገባችሁ በላይ አድርጋችኋል”ወይም “ሊኖራችሁ ከሚገባው በላይ የሆነ ሥልጣን ያላችሁ ይመሰላችኋል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)