am_tn/num/16/01.md

1.9 KiB

ቀአት

የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

በሙሴ ላይ ተነሱ

በአንድ በኃላፊነት በሚገኝ ሰው ላይ ማመፅና መተቸት ልክ ለመጣላት እንደተነሱ ዓይነት ነገር ተደርጎ ተገልጿል፡፡“በሙሴ ላይ አመፁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሁለት መቶ ሃምሣ

“250”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ታዋቂ የሆኑ የማህበረሰቡ አባላት

“ዝነኛ የሆኑ የማህበረሰቡ አባላት” ወይም“በማህበረሰቡ ውስጥ ዋና የሆኑ ሰዎች”

እናንተ እጅግ አብዝታችኋል

ይሄ የሚያመለከተው አንድ ሰው ማድረግ ከሚገባው በላይ ማድረጉን ነው፡፡“ማድረግ ከሚገባችሁ በላይ አድርጋችኋል”ወይም “ሊኖራችሁ ከሚገባው በላይ የሆነ ሥልጣን ያላችሁ ይመሰላችኋል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር ጉባዔ ላይ ለምን ትታበያላችሁ?

ሰዎቹ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቁት ሙሴንና አሮንን ለመገሰፅ ብለው ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “በተቀረው የእግዚአብሔር ጉባዔ ላይ ራሣችሁን ከፍ ማድረጋችሁ ትክክል አይደለም” (ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሌሎቹ በላይ ራሣችሁን ከፍ ማድረጋችሁ

አንድ ሰው አስፈላጊ ነኝ ብሎ የማመኑን ነገር ራስን ከፍ ከማድረግ ጋር ተነፃፅሯል፡፡“ራሣችሁን ከሌሎች የበለጠ አስፈላጊ ነን ብላችሁ ትገምታላችሁ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)