am_tn/num/15/37.md

1.5 KiB

የእሥራኤል ትውልዶች

“የእሥራኤል ሕዝብ”

ተግባራዊ ለማድረግ

“እነርሱን ለመታዘዝ”

የልባችሁንና የዓይኖቻችሁን ፈቃድ እንዳትመለከቱ

እዚህ ላይ “መመልከት”የሚለው ቃል ማሰብ ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ልብ አንድ ሰው የሚሻውን ነገር የሚያመለክት ሲሆን ዓይን ደግሞ አንድ ሰው የሚያየውንና የሚፈልገውን ነገር ያመለክታል፡፡“የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ እንዳታስቡ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

እርስዋን በመከተል ያመነዘራችሁበትን

ልባቸው ያሻውን ነገር እያደረጉ እግዚአብሔርን ያለመታዘዛቸውን ሁኔታ አንዲት ሴት ለባልዋ ታማኝ ካለመሆኗ የተነሣ ከሌላ ሰው ጋር ዝሙት እንደምትፈፅም ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡ይሄ አሣፋሪ ድርጊት ስለመሆኑ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“በሚያሣፍር ሁኔታ ለእኔ ታማኝ አልሆናችሁም”ወይም “ከመታዘዝ ይልቅ እነዚሀን ነገሮች ታደርጋላችሁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን፤በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)