am_tn/num/15/22.md

1.4 KiB

ማያያዣ ዓረፍተ ነገር

እግዚአብሔር ሙሴ ለእሥራኤል ሕዝብ መናገር ስላለበት ነገር መናገሩን ይቀጥላል፡፡

አጠቃላይ መረጃ

እዚህ ላይ “እናንተ” የሚለው ቃል የሚመለክተው እሥራኤላውያንን ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ የሚሆንን ነገር ለማቅረብ

“እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ ለማቅረብ” የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር በቅን ልብ መሥዋዕትን በሚያቀርብ ሰው መደሰቱን ለመግለፅ ልክ እግዚአብሔር በመልካም የሽቱ መሥዋዕት እንደሚደሰት ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ እርሱን በማቅረብ እግዚአብሔርን ማስደሰት፡፡”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን መደረግ ይኖርበታል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ማድረግ ይኖርባችኋል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ሕጉ

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሕጉ እንደሚያዘው”ወይም “ሕጉን ሳወጣ ባዘዝኩት መሠረት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)