am_tn/num/15/14.md

1.9 KiB

ቁርባንን በእሣት ማቅረብ ይኖርበታል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በመሠዊያው ላይ ቁርባንን ማቃጠል ይኖርበታል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ የሚሆንን ነገር ለማቅረብ

“እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ ለማቅረብ”የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር በቅን ልብ መሥዋዕትን በሚያቀርብ ሰው መደሰቱን ለመግለፅ ልክ እግዚአብሔር በመልካም ሽቱ መሥዋዕት እንደሚደሰት ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እርሱን በማቅረብ እግዚአብሔርን ማስደሰት፡፡”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእናንተም መካከል ለሚቀመጥ መፃተኛ አንድ ሥርዓት ይሆናል

ለዚህ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት1/ “እናንተና በመካከላችሁ ያሉት መፃተኞች በእግዚአብሔር ፊት እኩል ናችሁ”ወይም “እናንተንም ሆነ መፃተኛውን የሚገዛው ሕግ ተመሳሳይ ነው”

እናንተ እንደምታደርጉት እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት ያደርጋል

እናንተ እንደምታደርጉት እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት የሚያደርጉበት ምክኒያት በእግዚአብሔር ፊት እንደ እሥራኤላውያን መሆን ያለባቸው በመሆኑ ነው፡፡ይሄ የሚያመለክተው ሕጎቹን ሁሉ እንደ እሥራኤላውያን መጠበቅ አለባቸው ማለት ነው፡፡እናንተ እንደምታደርጉት ማድረግና ሕጎቹንም ሁሉ መጠበቅ ይኖርባቸዋል”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)