am_tn/num/14/41.md

2.2 KiB

የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ?

ሙሴ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው የእሥራኤልን ሕዝብ ለመገሰፅ ነው፡፡ይሄ አሕፅሮተ ሥም በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንደገና መተላለፍ የለባችሁም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር በእናንተ መካከል አይደለም

እነርሱን ማገዝ ከእነርሱ ጋር እንደመኖር ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እግዚአብሔር አይረዳችሁም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በጠላቶቸችሁ ፊት እንዳትወድቁ

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ጠላቶቻችሁ ድል እንዳይነሷችሁ ለመከላከል” ወይም “በጠላቶቻችሁ ላይ ድልን እንድታገኙ ለማድረግ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰይፍ ትወድቃላችሁ

እዚሀ ላይ “ሠይፍ”የሚያመለክተው ጦርነትን ነው፡፡“በጦርነት ውስጥ ትሞታላችሁ”ወይም “ከእነርሱ ጋራ ስትዋጉ ይገድሏችኋል” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋልና

እግዚአብሔርን መታዘዝ እርሱን እንደ መከተል ተደርጎ የተገለፀ ሲሆን የሚናገረውን ቃል አለመፈፀም ደግሞ ከእርሱ እንደመመለስ ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እግዚአብሔርን መታዘዝ አቁማችኋል”ወይም “እግዚአብሔርን ላለመታዘዝ ወስናችኋል” “(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)”

ከእናንተ ጋር አይሆንም

እነርሱን ማገዝ ከእነርሱ ጋር እንደመኖር ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡“አይረዳችሁም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)