am_tn/num/14/01.md

1.4 KiB

እግዚአብሔር በሰይፍ እንሞት ዘንድ ወደዚች ምፍር ለምን ያገባናል?

እዚህ ላይ ሰዎቹ ጥያቄ የሚያነሱት እግዚአብሔር በአግባቡ እንዳልያዛቸው ለመግለፅ ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በሠይፍ እንድንገደል ለማድረግ ሲል ብቻ እግዚአብሔር ወደዚህ ሥፍራ ሊያመጣን አይገባም ነበር” (ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በሠይፍ ለመገደል

እዚህ ላይ“ሠይፍ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሠይፍ መሞትን ወይም በጦርነት ውስጥ መሞትን ነው፡፡ “ሰዎች በሠይፍ ሲያጠቁን መሞት”ወይም “በጦርነት ውስጥ መሞት”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ግብፅ መመለስ አይሻለንምን?

ሰዎቹ ይሄንን ጥያቄ የሚጠይቁት ሌሎች ሰዎችም ወደ ግብፅ ብንመለስ ይሻለናል ብለው በሃሣባቸው እንዲስማሙላቸው ለማድረግ ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ከነዓንን ለማሸነፍ ከምንጥር ይልቅ ወደ ግብፅ ብንመለስ ይሻለናል”