am_tn/num/13/32.md

1.7 KiB

እነርሱ ስለ ሰለልዋትም … እያወሩ

እዚህ ላይ “እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከካሌብና ከኢያሱ በስተቀር በጊዜው ለስለላ የሄዱትን ሰዎች ሁሉ ነው፡፡

የሚኖሩባትን ምድር የምትበላ ምድር

ሰዎቹ ምድሪቱ ወይም በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች እጅግ አደገኞች መሆናቸውን ለመግለፅ ምድሪቱ ሰዎችን የምትበላ እንደሆነች አድርገው ያቀርቡታል፡፡“እጅግ አደገኛ ምድር”ወይም “ሰዎቹ ነፍሳችንን የሚያጠፉበት ምድር” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ዔናቅ

ይሄ የሰው ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ በዓይናችን ግምት …እኛ በዓይናቸው ዘንድ

እዚህ ላይ “ማየት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ግምገማንና የፍርድ ውሳኔ መሥጠትን ነው፡፡“በእኛ አስተሳሰብ…በእነርሱ አስተሳሰብ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በዓይናችን ግምት እንደ አንበጣ ነበርን

ሰዎቹ ስለ አንበጣ የተናገሩት በዚያ ምድር ካሉት ሰዎች ጋር ራሣቸውን ሲያነፃፅሩ ምን ያሀል ትንሽ መሆናቸው እንደተሰማቸው ለመግለፅ ብለው ነው፡፡“እኛን ከእነርሱ ጋር ስናነፃፅረው የአንበጣ ያህል ትናንሾች ነን›፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)