am_tn/num/10/10.md

2.0 KiB

በዓልን ማክበር

“መከበር”የሚለው ስም “ማክበር”በሚለው ግሥ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በምታከብሩበት ወቅት”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)

መለከቱን መንፋት ይኖርባችኋል

እዚህ ላይ እግዚአብሔር ለሙሴ ቢናገርም በመሠረቱ ካህናቱ መለከቱን እንዲነፉ ነው የፈለገው፡፡“ካህናቱ መለከቱን እንዲነፉ ትዕዛዝ መሥጠት ይኖርብሃል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

በወሩ መጀመሪያ

በዕብራውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት አሥራ ሁለት ወራት አሉ፡፡በብርማ ቀለም የሚደምቀው የጨረቃ በርሃን የመጀመሪያው ምዕራፍ በቀን አቆጣጠሩ ላይ የመጀመሪያው ወር መሆኑን ያመለክታል፡፡(የዕብራውያን ወራት የሚለውን ይመልከቱ)

የሚቃጠል መሥዋዕታችሁ…የደህንነት መሠሥዋዕታችሁ…እናንተ ለእኔ

በእነዚህ ሐረጎች ውስጥ “እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር በመሆኑ የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝበ ነው፡፡(እናንተ ለሚለው ቃል የተለያዩ አገላለፆች የሚለውን መልከቱ)

መሥዋዕታችሁ ላይ

“ለመሥዋዕቱ ከብር”

እነርሱም ለመታሰቢያ ይሆኑላቸኋል

“ለእኔ መታሰቢያ ይሆናችኋል” “መታሰቢያ”የሚለው ቃል “መታሰብ”በሚለው ግሥ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እኔን እንድታሰቡ ያደርጋችኋል”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱም ይሆኑላችኋል

“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው መለከቶቹንና መሥዋዕቶቹን ነው፡፡