am_tn/num/09/13.md

2.5 KiB

ንፁህ የሆነ ማንኛውም ሰው

እዚህ ሥፍራ ላይ እግዚአብሔር አንድን ሰው በመንፈሣዊ ሕይወቱ ተቀባይነት እንዳለው የሚቆጥረውን ሰው ልክ ሰውነቱ ንፁህ እንደሆነ ተደርጎ ይገለፃል፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ፋሲካን ጠብቁ

“ጠብቁ”የሚለው ቃል ትኩረት ስጡት ማለት ነው፡፡ “ፋሲካን በአግባቡ ትኩረት ስጡት”ወይም “ፋሲካን አክብሩት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሰውዬው መቆረጥ ይኖርበታል

እዚህ ላይ “መቆረጥ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ንብረቱን መንጠቅና ማባረርን ነው፡፡ “ያ ሰው መባረር ይኖርበታል”ወይም “ያንን ሰው ማባረር ይኖርባችኋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

አቋም መያዝ

አቋም መያዝ ወይም አስቀድሞ መወሰን፡፡

ያ ሰው ኃጢአቱን መሸከም ይኖርበታል

እዚህ ላይ አንድ ሰው የኃጢአትን ውጤቶች መሸከም እንዳለበት የሚገልፀውን ሃሣብ ኃጢአቱን እንደ ዕቃ እንደሚሸከመው ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ያ ሰው የኃጢአቱን ቅጣት መሸከም ይኖርበታል”

በእናንተ መካከል ይኖራል

እዚህ ላይ “እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡(እናንተ የሚለውን የተለያዩ አገላለፆች የሚለውንይመልከቱ)

ትዕዛዛቱን ሁሉ መጠበቅና ማድረግ ይኖርበታል

“ያ መፃተኛ ሰው እግዚአብሔር የሚያዝዘውን ትዕዛዛት መጠበቅና ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል”

የፋሲካን ሥርዓት ይጠብቅና ሕጉን ይታዘዝ ዘንድ

በመሠረቱ እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ሁለቱ ሐረጎች እንዲቀናጁ የተደረጉበት ምክኒያት መፃተኛው የፋሲካን ሕጎች በሙሉ መታዘዝ እንደሚኖርበት አፅንዖት ለመሥጠት ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

በምድሩ ውስጥ

“በእሥራኤል ምድር ውስጥ”