am_tn/num/08/18.md

1.2 KiB

በበኩራቱ ፋንታ …ሌዋውያንን ወስጃለሁ

“ወስጃለሁ” የሚለው ቃል በመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር ግልፅ ሲሆን በሁለተኛውም እንዲሁ ሊደገም ይችላል፡፡“በኩሮቹን ከመውሰድ ይልቅ…ሌዋውያንን በሙሉ ወስጃለሁ”(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)

ሌዋውያንን ለአሮንና ለልጆቹ ሥጦታ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ

እግዚአብሔር ሌዋውያን አሮንና ልጆቹን እንዲያግዟቸው የመደበበትን ሁኔታ ልክ እግዚአብሔር ለአሮንና ለልጆቹ እንደ ሥጦታ እንደሰጣቸው ተደርጎ ሲነገር እናያለን፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱን ወስጃቸዋለሁ...እነርሱን ሰጥቻቸዋለሁ

እዚህ ላይ “እነርሱን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሌዋውያንን ነው፡፡

እነርሱ በሚቀርቡበት ወቅት

እዚህ ላይ “እነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡