am_tn/num/08/16.md

1.4 KiB

በኩራት ሁሉ፤ማሕፀን የሚከፍት ሁሉ

በመሠረቱ እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በጋራ እንዲነገሩ የተደረገው በኩር ልጆችን በተመለከተ የበለጠ አፅንዖት ለመስጠት ሲባል ነው፡፡ (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ማሕፀንን የሚከፍት ወንድ

ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“ማሕፀንን የሚከፍት” ማለት ለመጀመሪያ ጊዜ ልጅን የሚወልድ ማለት ነው፡፡ይሄ የሚያመለክተው እናት ለመጀመሪያ ጊዜ የምትወልደውን ወንድ ልጅን ነው፡፡“ለእናቱ የመጀመሪያ ሆኖ የተወለደ ወንድ ልጅ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሕይወታቸውን ነጠቅኩ

ይሄ አንድ ሰው ሌላ ሰውን በሚገድልበት ወቅት የሚገለፅበት የትህትና አነጋገር ነው፡፡“ገደልኩ”(ሥርዓት የሌለውን ነገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱን ለእኔ ለይቻቸዋለሁ

እዚህ ላይ “እነርሱን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው “በእሥራኤል መካከል የተወለዱትን በኩሮች ነው”