am_tn/num/07/84.md

3.9 KiB

እነዚህን ሁሉ ለዩልኝ

“መለየት”የሚለው ሐረግ ለአንድ ለተወሰነ ዓላማ ራስን መሥጠት ማለት ነው፡፡በዚህ መሠረት ሥጦታዎቹ የሚሰጡት ለእግዚአብሔር ነበር፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሙሴ መሠዊያውን በቀባበት ቀን

እዚህ ላይ“ቀን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በአጠቃላይ ዘመኑን ነው፡፡የእሥራኤል አለቆች እነዚህን ነገሮች በአሥራ ሁለት ቀናት ነበር የሚሰውት፡፡ “ሙሴ መሠውያውን በቀባበት ወቅት”

130 ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የብር ወጭት

አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ 430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝን ነበር

“እያንዳንዱ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝን ነበርይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”እያንዳንዱ የብር ድስት አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ድስት 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

2,400 ሰቅል

“ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል”ወይም “ሃያ አራት መቶ ሰቅል”

በቤተመቅደሱ የሰቅል ሚዛን መሠረት

የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የጥራት ደረጃ መሠረት የተመዘነ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)

የብር ዕቃዎቹ ሁሉ ተመዘኑ…የወርቅ ዕቃዎቹ ሁሉ ተመዘኑ

“የብር ዕቃዎቹ ሁሉ በአንድ ላይ ተመዘኑ…የወርቅ ዕቃዎቹ ሁሉ በአንድ ላይ ተመዘኑ”

የብር ዕቃዎቹ ሁሉ

እነዚህ የሚያመለክቱት ከብር የተሰሩትን በሳህንና በወጭት መልክ የመጡትን ሥጦታዎች ነው፡፡

እንዳንዳቸው አሥራ ሁለቱ የወርቅ ሣህኖች …አሥር ሰቅል ይመዝኑ ነበር

“እንዳንዳቸው አሥራ ሁለቱ የወርቅ ሣህኖች …10 ሰቅል ይመዝኑ ነበር፡፡አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”እያንዳንዳቸው 12 የወርቅ ሣህኖች…. አንድ አሥረኛ ኪሎግራም ይመዝኑ ነበር”ወይም “እንዳንዳቸው 12ቱ የወርቅ ሣህኖች 110 ግራም ይመዝኑ ነበር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

120 ሰቅል

“አንድ መቶ ሃያ ሰቅል” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)