am_tn/num/06/05.md

1.5 KiB

ራስን ለመለየት ስእለት ማድረግ

ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“መለየት”ማለት“ራስን መስጠት”ማለት ነው፡

በራሱ ላይ ምላጭ መድረስ አይኖርበትም

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ማንም ሰው ቢሆን በራሱ ላይ ምላጭ መጠቀም የለበትም”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት

“መለየት” የሚለው ቃል አሕፅሮተ ሥም ሲሆን በግሥ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡እዚህ ላይ “መለየት”ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን “ለአንድ ነገር ራስን መስጠት ማለት ነው”“ራሱን ለእግዚአብሔር የለየበት ወራት”ወይም “ራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠበት ወራት”(አሕፅሮተ ሥምንና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈፀም ድረስ

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለእግዚአብሔር የሚለይበት ወራት የመጠናቀቂያ ጊዜ አለው ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእግዚአብሔር መለየት ይኖርበታል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሱን ለእግዚአብሔር መለየት አለበት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)