am_tn/num/05/27.md

2.2 KiB

ከፈፀመችው የተነሣ የረከሰች ከሆነ

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “ድርጊቱን ከመፈፀሟ የተነሣ የረከሰች ከሆነ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ኃጠአትን ሠርታለች

እዚህ ላይ “ኃጢአት”የሚያመለክተው በተለይ ዝሙት መፈፀምን ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ዝሙትን ሠርታለች” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሆድዋም ይነፋል፤ጭንዋም ይሰለስላል

ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1)ሴትዬዋ ልጅ ለመውለድ አትችልም 2)የሴትዋ ፅንስ ስለሚጨናገፍ ሕፃኑ ልጅ በሕይወት አይኖርም፡፡እዚህ ላይ “ጭን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሴትን ማሕፀን ወይም የአካሏን ክፍል ነው፡፡(ሥርዓት የሌለውን ነገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ) ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 5፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

ሴቲቱም በሕዝብዋ መካከል ለመርገም ትሆናለች

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሕዝቧ ይረግማታል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ያልረከሰች

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አላረከሳትም”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ንፁህ ከሆነች

እዚህ ላይ “ጥፋተኛ አለመሆን” “ንፁህ መሆን” በሚል ቃል ይገለፃል፡፡ (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ንፁህ ትሆናለች

ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1)“ከዚያ በኋላ የተረገመች አትሆንም”2)“ከዚያ በኋላ ከመርገም ነፃ ትሆናለች”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ልጅንም ታረግዛለች

“ታረግዛለች”