am_tn/num/05/20.md

2.8 KiB

በባሏ ሥር

ይሄ ሐረግ የሚያመለክተው በባሏ ሥልጣን ሥር መሆኗን ነው፡፡“በባሏ ሥልጣን ሥር” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

የራሳችሁን መንገድ ካልተከተላችሁ

“የራስን መንገድ መከተል”የሚለው ሐረግ ምሣሌያዊ አነጋገር ሲሆን “ታማኝ አለመሆን”ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ረክሳችኋል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሣችሁን አርክሳችኋል” (ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

በላይዋ ላይ መርገምን ሊያወርድ የሚችል

“መርገምን ሊያወርድ”የሚለው ቃል ምሣሌያዊ አነጋገር ሲሆን በላይዋ ላይ መርገም ይመጣል የሚል ፍቺ ያለው ነው፡፡“በላይዋ ላይ መርገም እንዲመጣ ሊያደርግ የሚችል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ለእርግማን ይዳርግሻል…በሕዝብሽ መካከል

እዚህ ላይ ፀሐፊው የሚናገረው ሌሎች ሰዎች እንዲረግሟት መንስኤ የሚሆነውን እግዚአብሔር ለሴትዬዋ የሚሰጣትን መርገም በተመለከተ ልክ ሴትዬዋ ራስዋ መርገም እንደሆነች አድርጎ ነው የሚገልፀው፡፡“እግዚአብሔር የረገመሽ በመሆኑ ሌሎች ሰዎችም ይረግሙሻል፡፡እግዚአብሔርም በእውነት ስለመረገምሽ ሰዎች እንዲመለከቱ ያደርጋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በዚህ መልኩ ለሕዝብሽ የሚታይ ይሆናል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”ይህንን ለሕዝብሽ እንደ እርግማን ያሣየዋል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ይሄ በሕዝብሽ መካከል የሚደረግ ይሆናል

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡1)ሴትዬዋ ልጅ ለመውለድ አትችልም 2)እርግዝናው የሚጨናገፍ በመሆኑ ሕፃኑ ልጅ በሕይወት አይኖርም፡፡

ጭንሽ ይሰለስላል

እዚህ ላይ “ጭን” የሚለው ቃል የሴትን ማሕፀን ወይም ሌላ የሰውነት አካሏን ለመጥራት የተጠቀሙበት ጨዋ የሆነ አገላለፅ ነው፡፡“ማሕፀንሽ ጥቅም የማይሰጥ ይሆናል”(ሥርዓት የሌለውን ነገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ)