am_tn/num/05/18.md

1.6 KiB

በእግዚአብሔር ፊት

“በእግዚአብሔር ሕልውና ፊት”

በሚቀርበው የእህሉ ቁርባን

ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 5፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

የራሳችሁን መንገድ ካልተከተላችሁ

“የራስን መንገድ መከተል” ምሣሌያዊ አነጋገር ሲሆን “ታማኝ አለመሆን”ማለት ነው፡፡ “ለባለቤትሽ ታማኝ ካልሆንሽ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኃጢአትን ፈፀማችሁ

“ኃጢአትን በመፈፀም” ይሄ ሐረግ የሚያመለክተው “ዝሙትን ስለመፈፀም ነው”

ከዚህ መራራ ውኃ ነፃ ትሆናላችሁ

ከሆነ ነገር “ነፃ ትሆናላችሁ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በእርሱ አለመጎዳትን ነው፡፡“ሊጎዳችሁ የሚችል ውኃ ለጉዳት አይሰጣችሁም”(ምሣሌያዊ አነጋገርን የሚለውን ይመልከቱ)

መርገምን ሊያመጣ የሚችለው ይሄ መራራ ውኃ

እዚህ ላይ መራራው ውኃ መርገምን ሊያመጣ እንደሚችል ተደርጎ ተገልጿል፡፡ይሄ ማለት አንዲት ሴት ኃጢአተኛ ከሆነች ውኃውን በምትጠጣበት ወቅት ልጅ እንዳትወልድ ምክኒያት ይሆንባታል ማለት ነው፡፡“ይሄ መራራ ውኃ መርገም ሊሆንብህ ይችላል”(ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)