am_tn/num/05/01.md

1.4 KiB

ተላላፊ የቆዳ በሽታ

ይሄ የሚያመለክተው ቆዳን ለበሽታ የሚዳርገውንና ወደ ሌሎች ሰዎች በፍጥነት የሚዛመተውን የቆዳ በሽታ ነው፡፡

ለሕመም የሚዳርግ ፈሳሽ

ይሄ የሚያመለከተው ከተከፈተ ነገር ውስጥ የሚወጣን ፈሳሽ ነው፡፡

በሬሣም የረከሰውን ሁሉ

አንድ ሰው ሬሣ የሚነካ ከሆነ እንደረከሰ ነበር የሚቆጠረው፡፡የእግዚአብሔርን ዓላማ ለማስፈፀም ተቀባይነት የሌለው ሰው አካሉ ንፁህ እንዳልሆነ ተደርጎ ነው የሚገለፀው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ አውጧቸው

እዚህ ላይ “እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር በመሆኑ የእሥራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ነው፡፡

የእሥራኤልም ልጆች እንዲሁ አደረጉ

ይሄ ማለት የረከሱትን ሰዎች አስወጧቸው ማለት ነው፡፡የዚህ ሙሉ ሃሣቡ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“የእሥራኤል ሰዎች የረከሱትን ሰዎች ከሠፈራቸው ውጪ እንዲወጡ አደረጓቸው”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)