am_tn/num/04/24.md

1.1 KiB

ይሄ የነገዶች ሥራ ነው….በሚያገለግሉበትና በሚሸከሙት ነገር

ይሄ ዓረፍተ ነገር የሚቀጥሉት ቁጥሮች ስለ ምን እንደሚናገሩ መግለጫ የሚሰጥ ነው፡፡

ጌድሶናውያን

ይሄ የሚያመለክተው የጌድሶናውያንን ትውልድ ነው፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 3፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

በላዩም ያለውን የአስቆጣውን ቁርበት

ይሄ በመገናኛው ድንኳኑ ላይ የሚደረግ የውጪ ሽፋን ነው፡፡“በዚያ ላይ የሚደረግ የአስቆጣ ቁርበት”ወይም “በአስቆጣ ቁርበት የሚሰራ የላይኛው መሸፈኛ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በእነዚህ ነገሮች የሚደረጉ ነገሮች ሁሉ

ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለእነዚህ ሥራዎች የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)