am_tn/num/04/17.md

1.2 KiB

የቀአት ወገኖች

ይሄ የሚያመለክተው የቀአትን የዘር ሐረግ ነው፡፡በኦሪት ዘኁልቁ 3፡27 ላይ ይሄንን እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

ከሌዋውያን መካከል መጥፋት

ይሄ ሐረግ የሚያመለክተው የቀአታውያንን ሞት ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “ከሌዋውያን ወገን ፈፅሜ እንዳጠፋቸው ምክኒያት የሚሆኑትን ነገሮች የሚያደርጉትን ሁሉ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህንን በማድረግ

ይሄ ሐረግ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ቀጥሎ ስለሚናገረው ነገር ነው፡፡ሙሴ ቀአታውያን እንዳይጎዱ ለመከላከል ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ እንዳይገቡ ያግዳቸዋል፡፡

ለሥራውና ለተለየ ተግባሩ

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ተቀናጅተው የቀረቡትም ለጉዳዩ አፅንኦት ለመስጠት ሲባል ነው፡፡